ይህ ታሪካዊ የቱሪስት መዳረሻ ከወረዳው ማዕከል 33 ኪ.ሜ ርቅት ላይ የሚገኘኝ ሌላኛው የማጂ አስደማሚ ሰው ሰራሽ ታሪካዊ መስህብ ነው፡፡
ይህ ንፋስ በር የተሰኘው ድንቅ መስህብ ከታሪካዊ አፈጣጠሩ ጀምሮ በግርምት የሚሞላ የድንቅ ታሪካዊ አሻራ ባለቤት የሆነ መስህብ ነው፡፡
የንፋስ በር አፈጠጠርን ለየት የሚያደርገው የፋሺስት ጣልያን ሃገራችን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ለከባድ መሳሪያዎቹ መጓጓዣነት በሁለት ከፍተኛ ተራሮች መካከል የሚገኙ አለቶችን በመሳሪያ በመደምሰስ እና በመካከል ያለውን ክፍተት በአለቶች በመሙላት ያበጀው ቀጭን የሰውና የተሸከርካሪ መተላለፊያ መንገድ ነው፡፡
ምንም አይነት ዘመናዊ የግንባታም ሆነ የመሰረተ ልማት ግበአት በሌለበት በዚያ ዘመን ይህንን በመሰለ መልኩ ሁለት ግዙፍ ተራሮችን/ስፍራዎችን በአለት ድልድይ ለማገናኘት ምን አይነት መንፈሳዊ ጽናትና ትጋትን እንደሚጠይቅ ንፋስ በርን በስፍራው ተገኝቶ ያላየ ሰው እንዴት ሊረዳው ይችላል?