ይህ መስህብ ከወረዳ ማዕከል መነሻ ካደረግን 100ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል መገኛውም በሙይ/ኦሞ ፓርክ ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህም ሌላኛው አሰደማሚ የማጂ ውብ ገፀበረከት ነው፡፡
ንፁህ የተፈጥሮ ኩሬ ዉሃ ምንም አይነት እሳትም ሆነ ሰው ሰራሽ የሙቀት አመንጪ ሃይል በሌለበት ስፍራ ልክ በብረት ድስት ተጨምሮ የጎፈጠጠ ፍም ላይ ተጥዶ እንደሚፍለቀለቅ የብረት ድስት ዉሃ ሲፍለቀለቅ ማየት ከፈለጉ ወደ ሙይ ፓርክ እግሮን ማንሳት ነው፡፡
ይህ ፍል ውሃ ከመስህብነት በተጨማሪ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን በዋነኝነት በጤናው መስክ ያለውን ፋይዳ ብንመለከት ለበርካታ አካላዊና ውስጣዊ ደዌዎች ፈውስ በመሆን እንደሚያገለግል ተጠቃሚዎች ይመሰክራሉ፡፡