ዲዚኛ English አማርኛ
Diizi and Diizi Area Scholars

የጣሊያን ጡብ ቤቶች

August 30, 2025 1.2K Views 5 min read Historical Sites Maji
የጣሊያን ጡብ ቤቶች

ይህ የጣሊያን ጡብ ቤት የተሰኘው ውድ ቅርስ ማጂ ከተሸከመቻቸው በርካታ አስገራሚ ታሪካዊ አሻራዎች አንዱ ነው፡፡ይህ የጣሊያን ጡብ ቤት ከመጠሪያ ስሙ �ንደምንረዳው ፋሽስት ጣሊያን ሃገራችን ኢትዮጵያን በወረረበት በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አንድ ዓ.ም ያነፀው ጥንታዊ የስነ ህንጻ ጥበብ ውጤት ነው፡፡በወቅቱ ፋሽስት ጣልያን �ደማጂ የገባው በ1930ዓ.ም ሲሆን ከዚያ በኋላ ለቆየባቸው ሶስት አመታት በሶስት የተለያዩ ስፍራዎች እነዚህን ቤቶች ገንብቶ ለተለያዩ አላማዎች ይጠቀምባቸው እንደነበር የታሪክ አዋቂዎች ምስክርነት ያስረዳል፡፡በዋነኝነትም በማጂ ለውጥ ፍሬ ት/ት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚገኘውን ለመኖሪያ ቤትነት፤በማጂ ማዘጋጃ ቤት �ጥር ጊቢ የሚገኘውን ለአስተዳደር ቢሮ እንዲሁም በማጂ ፖሊስ ጣቢያ ቅጥር ጊቢ የሚገኘው ደግሞ ለግምጃ ቤትነት(ለመጋዝንነት) ይጠቀሙበት እንደነበር ለማጂ ዕድሜ ጠገብቶች እንደ የሩቅ ቅርብ ትዝታቸው ነው፡፡

በዚህ በጣሊያን ጡብ ቤት ላይ ከምናገኛቸውና ጥንታዊውን የስነ �ህንጻ ጥበብ ልቀት ከሚያሳዩን እፁብ ገፅታዎች አንዱ ይህ ቤት ሲገነባ ለጡቡ(ለግድግዳው)ማያያዣ እንደ ሲሚንቶ የተጠቀመው ንፁህ ቀይ አፈር መሆኑ ነው፡፡ይህም ብቻ ሳይሆን ይህን ቅርስ እና ጥንታዊውን የነጮች �ነስነ ህንፃ ጥበብ አስገራሚ የሚያደርገው ትላንት በዘመናዊ የግንባታ ጥበብ ተገንብተው የምናውቃቸው ቤቶች በማግስቱ ከመሰረታቸው ጀምሮ መሰነጣጠቅ እና መፈራረሳቸውን በለመድንበት በዚህ ዘመን ይህ ቤት ግን ወደ መቶ ለሚጠጉ በርካታ አስርት አመታት ዛሬም እንደነበረው ከነሙሉ ግርማ ሞገሱ ቆሞ መመልከት መቻላችን ነው፡፡ይህ ቤት በማጂ 01 ቀበሌ በሶስት የተለያዩ ስፍራዎች ማለትም በማጂ ለውጥ ፍሬ 2ኛ �ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት፤በማጂ ማዘጋጃ ቤትና፤ በማጂ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኝ ሲሆን እጅግ በጥቂቱ በማጂ ማዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ የሚገኘው ቤት በ2000ዓ.ም ከተደረገለት ውስን የእድሳት ሙከራ በስተቀር በሶስቱም ስፍራዎች የሚገኙ እነዚህ የጣሊያን ጡብ ቤቶች ከተገነቡ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ምንም አይነት እድሳትም ሆነ ልዩ ጥበቃ አልተደረገላቸውም፡፡
እነዚህ የጣልያን ጡብ ቤቶች በቅርበት እና በከተማ ውስጥ መገንባታቸው ለቱሪስትም ሆነ ለየትኛውም ጎብኚ አካል �ቹ ያደርጋቸዋል፡፡ስለሆነም ይህንን �ጋጣሚ በመጠቀም ይህንን ውድ የማጂ ዕድሜ የመላይቷ ሃገራችንን የታሪክ አሻራ የተሸከመ ውድ ታሪካዊ ቅርስ ታሪካዊ ህልውናውን በማይነካና በማያጠፋ መልኩ ለማደስ፤ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ ብሎም ለትውልድ ለማስተላለፍ ማንኛውም የሚመለከተው የግልም ሆነ የመንግስት አካል እኛ፤እነሱ ሳንል ሁላችንም በመተባበር እና አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት ይህንን እና ሌሎችም መሰል ታሪካዊ የማጂ ቅርሶች ከጥፋት እንታደግ �ሲል የማጂ ወረዳ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ጽ/ቤት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

Historical Sites Share:
Back to All Maji Tourism