ዲዚኛ English አማርኛ
Diizi and Diizi Area Scholars

አኩ/ሚሽን ፏፏቴ

October 22, 2025 1.2K Views 5 min read Nature Maji
አኩ/ሚሽን ፏፏቴ

ይህ የአኩ ፏፏቴ በወረዳችን ከሚገኙ በርካታ የቱሪስት መስህቦች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን ምሽን ፏፏቴ የተባለበትም ምክንያት በ1950ዎቹ አሜሪካውያን ምሽነሪዎች ይኖሩበት ስለነበር ነው፡፡ ይህ ፏፏቴ 70 ሜትር ርዝመትና 15 ሜትር ስፋት አለው፡፡ከማጂ ከተማ በቅርብ ርቀት/ 3 ኪ.ሜ / ስለሚገኝ ለጎብኝዎች / ለቱሪስቶች ምቹ ከመሆኑ ባሻገር ፏፏቴው የሚገኝበት ቦታ በተፈጥሮ የታደለ ስለሆነ እርሶ ይህን ቦታ ሲያዩ/ ሲጎበኙ ተፈጥሮን ያደንቃሉ፣ለተፈጥሮ ይማረካሉ፣በተፈጥሮ ይገረማሉ፣ይደመማሉ፣ በአረንጓዴ ደን ታጅቦ ከ70 ሜትር ከፍታ እየተምዘገዘገ ቁልቁል የሚፈሰው ውሀ እንደ አራስ ነብር በሚያስገመግም ድምጽ ታጅቦ ሲፈስ ልዩ ግርማ ሞገስ ያላብሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከከፍታ የሚፈሰው ውሀ አለቱ/ድንጋዩ ላይ ሲላተም በሚፈጥረው ፍንጣሬ የአካባቢውን የአየር ንብረት ከተፈጥሮ ውጭ የደርገዋል፡፡

ፏፏቴውን ከግራና ቀኝ ከበው አይዞህ ከጎንህ ነን የሚሉት ተራራና ሸንተረር ለፏፏቴው ልዩ ግርም ሞገስ አላብሰውታል፡፡ የፏፏቴውን ተፋሰስ ተከትለው ጥቂት ከተጓዙ በርካታ ስብሰባዎችን በአንዴ ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ዋሻ ያገኛሉ፡፡ ወደ ዋሻው ለመግባት ግን ባትሪ ወይም ተጨማሪ ብርሀን መያዝ ግድ ይላል፡፡ ፏፏቴው ጋ ከመድረሶ በፊት አቋርጠው የሚሄዱት የሚሽን መንደርም ተጨማሪ ገጽታ ነው፡፡

የሚገኝበት ቀበሌ፡- ማጂ 01

ከወረዳው ማእከል ከቱም ያለው ርቀት ፡- 22 ኪ.ሜ

የሚገኝበት ቦታ/ልዩ መጠሪያ ፡- ምሽን ሰፈር አካባቢ

ከከተማው/ከማጂ ያለው ርቀት ፡- 5 ኪ.ሜ

የሚፈጀው/የሚወስደው ሰዓት ፡- 15 ደቂቃ/በእግር

የፏፏቴው ርዝመት/ከፍታ ፡- 70 ሜትር

የፏፏቴው ስፋት ፡- 15 ሜትር

የመስህቡ ተደራሽነት /የትራንስፖርት ሁኔታ ፡- አስቸጋሪ/ በእግር

ለአካባቢው ህ/ብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ/ጠቀሜታ የሚሰጠው አገልግሎት ፡- ከቱሪስት መስህብነት በተጨማሪ ከአመታት በፊት ለእህል ወፍጮና ለሀይድሮ ኤሌትሪክ እንደሚያገላግል፤
በፏፏቴው አቅራቢያ/ዙሪያ ሚገኑ ተጨማሪ መስህቦች፡-ከፏፏቴ በስተቀኝ አነስተኛ ፏፏቴ፣ዋሻ፣የሚሽን ሰፈር ወዘተ…..

ሕይወት ግን የተፈጥሮ ቀመሯን ጠብቃ/ይዛ ጉዞዋን ትቀጥላለች እኛም ጉዞአችንን፡፡ ‹‹ቱሪዝም ያበለጽጋል፡፡

Nature Share:
Back to All Maji Tourism