ዲዚኛ English አማርኛ
Diizi and Diizi Area Scholars

ኮልቡ ደን

August 30, 2025 1.2K Views 5 min read Nature Maji
ኮልቡ ደን

ኮልቡ ደን ከወረዳ ማዕከል 28 ከ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በወረዳው ከሚገኙ ተፈጥሮዓዊ የቱሪስት መዳረሻዎች መሃል አንዱ ነው፡፡

የዚህ ደን ሽፋን በቻይት 332.9ሄ/ር፤በችግት 659.5ሄ/ር፤ ኩብት በኩል 1824.2ሄ/ር፤ በሀሮ በኩል 968.6ሄ/ር በጥቅሉ 2400ሄ/ር ሺፋን ሲኖረው ይህ በተፈጥሮ ህዝቡ በተለያዩ መንገዶች ጠብቆ ያቆየው ሀብት የተመልካች ቀልብ እጅግ ከሚስቡ ማራኪ ገፅታን በመላበስ የተመልካችን መንፈስ የሚያድሰ ውበት አለው፡፡

በውስጡ ገብቼ ልመልከት ላለ አካል ተፈጥሮ ውስጥ ሌላ መንፈሳዊ እረካታን ከማግኘቱ ባሻግር የተለያዩ እድሜ ጠገብ ዞፎችን ይመለከታል እነዚ ላይ የጉሬዛዎች ከዛፍ ዛፍ የሚያደርጉት ዝላይ ልዩ ስበት ይሰጣል፡፡

ሌሎች በደኑ ውስጥ የሚኖሩ የዱር እንስሳት እንደ ዱኩላ፤ከርከሮ፤ጅብ… ሌሎችን ጨምሮ ተሳቢ እንስሳት አና ለተለያዩ አዋፋትም ጭምር የመኖሪያ ቤታቸው ነው፡፡

Nature Share:
Back to All Maji Tourism