ዲዚኛ English አማርኛ
Diizi and Diizi Area Scholars

የጻና ፏፏቴ

August 30, 2025 1.2K Views 5 min read Nature
የጻና ፏፏቴ

የጻና ፏፏቴ የሚገኛው በቤሮ ወረዳ በካሲ ቀበሌ የተፈጥሮ ደን ውስጥ ሲሆን ስያሜውም በዲዚ ብሔረሰብ ቋንቋ ‹‹ጥቁር›› ማለት ነው፡፡ የዲዚ ብሔረሰብ ፏፏቴውን ጥቁር ያሉበት ምክንያት ደግሞ ከካሲ የተፈጥሮ ደን ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ፏፏቴውም በተፈጥሮ ደን መካከል ላይ የሚገኝ ሲሆን፡፡ በተለይ ደግሞ ፏፏቴው ከላይ ወደታች የሚወርድበት ድንጋይ ‹‹ጥቁር›› ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ነው ስያሜውን የሰጡት፡፡

ወደ ጻና ፏፏቴ ለመሔድ ቢያስፈልጎ ከጀባ ከተማ ወደ ካሲ ቀበሌ ከፈለጉ በሞተር ሳይክል 10 ደቂቃ ካልተመቾ በእግር ጉዞ ቢያንስ 40 ደቂቃ ያህል ከተጓዙ በኋላ ማጂ አግሮ ፎርስተሪ ቡና ልማት ተቋም( ያሁኑ ቶሞካ) ጋ ከወረዱ ወይም ከደረሱ በኋላ ዋናውን መንገድ ወደ ጎን በመተው በግራ በኩል በእግር መጓዝ ይጀምራሉ፡፡ ከዚያ ቢያንስ ከ10-20 ደቂቃ ከተጓዙ በኋል ከተፈጥሮ ደን ውስጥ ይደርሳሉ፡፡ በቀጥታ ቆልቁለቱን ከወረዱ በኋላ ወንዙን ይሻገሩና ወደ ጎን በመታጠፍ ወደፏፏቴው ይሂዳሉ፡፡ ማንም ሰው ሳያሳየዎት ወደፏፏቴው መሄድ ይችላሉ ለምን ቢሉ ከካሲ የተፈጥሮ ደን ውስጥ ያለውን ይህ ፏፏቴ ገና ከደኑ ሲደርሱ እዚህ ነኝ ይሎታል ፡፡

በካሲ የተፍጥሮ ደን ውስጥ ከጻና ፏፏቴ በተጨማሪ የዱር አራዊቶች ይገኛሉ፡፡ ከሚገኙትም መካከል አባጫኖ፣ጉሬዛ፣ዱኩላ፣ጅንጀሮ-- ወዘተ ከዚህ ከተፈጥሮ ደን ሳይገቡ ሁለት የተለያዩ ወንዞች ወደ ካሲ የተፈጥሮ ደን ውስጥ ይፈሳሉ፡፡ እነዚህ ከካሲ የተፈጥሮ ደን ውስጥ ተገኝተው የጻናን ፏፏቴ ይፈጥራሉ፡፡

የወንዙ ስም ኩዱምንቅ እና የል አይቅ ሲሆኑ መነሻቸውም ጀባ ት/ቤ ወንዝና ጋሮ የል ሐይቅ ራስ ነው፡፡ በተለይ ፏፏቴው ከታች ሁነው ቢመለከቱ ልዩ ግርምትን ይፈጥራል፡፡ ፏፏቴው ከላይ ወደታች ሲወርድ በአንድ ሳይሆን ሁለት ደረጃ አቋርጦ ነው የሚወርደው ፏፏቴው የሚወርድበት የተፈጥሮ ጥቁር ድንጋይ ልክ በድንጋይ የተገነባ ይመስላል፡፡ ዳሩ ግን ያው ተፈጥሮ የለገሰው ነው፡፡ ከፏፏቴው ወረድ ብሎ የተለያየ መጠን ያላቸው ድንጋዩች አረንጓዴ ለብሰው የተለያየ የሀርግ አይነቶች ልክ እንደ መሸጋገሪያ መስለው ከዚህ ወደዚያ የተዘረጉ የተፈጥሮ ሀብቶች በተለያዩ የወፎች ዝማሬና ከፏፏቴ ድምጽ ጋር ተደምረው ልዩ ውበት ይሰጣሉ፡፡ ወደ ፏፏቴው ከሄዱ ሁሉም ነገር የሰው እጅ ያልነካው የተፍጥሮ ደን ብቻ ስለሆነ ይማርኩታል ይጎብኙ ተደስተው ይመለሳሉ ማየት ማመን ነውና፡

Nature Share:
Back_to_All_Bero_Tourism