የሎሞት ዋሻ የሚገኘው በቤሮ ወረዳ በባይ-ባንካ ቀበሌ ሲሆን ከወረዳው ዋና ከተማ ጀባ በግምት 3.5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሆኖ ከዋናው መንገድ ኋላ በእግር የ10ደቂቃ ጉዞ የሚጠይቅ የተፈጥሮ ዋሻ ነው፡፡
በዚህም የዋሻው በር መግቢያ ላይ እንደደረስን በዋሻው ውስጥ የተለያዩ የዱር እንስሳት የሚገኙ መሆናቸውን የሚያመለክቱ አንድ አንድ ነገሮች የሚገኙ ሲሆን እነዚህም ነገሮች የጃርት እሾህ፣ ፀጉርና መንገዶች ናቸው፡፡
ከዚህም በተጨማር በዚህ ዋሻ ውስጥ አንደጃርት ፣ነብር፣ ቀበሮ፣አሳማ፣ ዘንዶና ሌሎችም እንስሳቶች ይኖሩበት እንደነበር ይነገራል፡፡
ይህ ዋሻ ልዩና ታርካዊ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ይህዋሻ መግቢያው በር ጠባብ ሲሆን ወደ ውስጥ ግን በጣም ሰፊና ውስጡም በጣም እሩቅና ወደውስጥም ትልቅ ወንዝ እንዳለና የዋሻው አቅጣጫም ሰሜንና ደቡብ አቅጣጫ የሚወስድ መንገድ እንዳለ አባቶች ይናገራሉ፡፡
ይይህ ዋሻ ከተፈጥሮአዊና አስደናቂነቱም በተጨማሪ በጣም ታሪካዊ የሚያደርገው በጥንት ዘመን የአከባቢው ነዋሪዎች እራሳቸውን ከጥላት ለመከላከልና ለማዳን ይደበቁበት እንደነበር ይነገራል፡፡