ይህም ሲባል ሜዳው በዙሪያው ያለው መልካዓ ምድራዊ አቀማመጡ እጅግ በጣም ገደላማና በተለያዩ ዋሻዎች የተከበበ በመሆኑ ሌሎች ቦታዎችን በሜዳው አናት ላይ ወጥቶ ለማየት አይከብድም ፡፡
መረጃ ሰጪዎች እንደሚሉት በዚህ ቦታ በጥንት ዘመን የሁለቱ አጎራባች ቀበሌ ወጣቶች ማለትም የዶንታና የባይ-ባንካ ቀበሌ ወጣቶች ትግል የሚያደርጉት ሲሆን ወጣቶች በእድሜ እኩያቸው ቢያንስ ከ15-20 አመት እድሜ ያላቸው ወጣቶች ናቸው ፡፡ እነዚህ ወጣቶች የሚታገሉት በቡድን ሲሆን ሰው ትግሉን በዳኝነት ይመራል ማለት ነው ፡፡
በትግሉ ወቅት ተሸናፊው ከተሸነፈ በኋላ ተቀምጦ ሌሎችን ትግሎችን የሚከታተል ሲሆን አሸናፊው ደግሞ ከሌሎች አሸናፊዎች ሰዎች ጋር የሚታገል ሲሆን ይህም ዝነኛ ወይም ስሙ እንዲሞገስ ያደርገዋል ማለት ነው፡፡
በትግሉ ወቅት ተሸናፊው ከተሸነፈ በኋላ ተቀምጦ ሌሎችን ትግሎችን የሚከታተል ሲሆን አሸናፊው ደግሞ ከሌሎች አሸናፊዎች ሰዎች ጋር የሚታገል ሲሆን ይህም ዝነኛ ወይም ስሙ እንዲሞገስ ያደርገዋል ማለት ነው፡፡
ይህ በእኩዮቹና በልጃገረዶች ዘንድ እጅግ ታላቅ ክብርና ዝና የሚያገኝ ሲሆን ይህ ወጣት በመጨረሻ የሁሉም አሸናፊ ከሆነ በኋላ የሌሎች ( አማካሪ) በመሆን ያገለግላል ፡፡ ይህም ትግል በመጨረሻ አሸናፊ የሆነው ወጣት ከሌላኛው ቀበሌ ወጣት ጋር ይታገላሉ፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ ያሸነፈ ወጣት በቀበሌው ስም የአሸናፊነት ስም ይሰጠዋል ማለት ነው ፡፡ ይህ ሲባል የዶንታ ወጣት ካሸነፈ ዶንታ አሸነፈ ሲባል የባይ-ባንካ ወጣት ካሸነፈ ደግሞ ባይ አሸነፈ ይባላል፡፡